ቀልብን ሰሊም ኔት ኢራን የሙስሊሙ አለም ቀንደኛ ጠላት ናት???ወይንስ ራሳቸውን የሱኒ መንግስታት ነን የሚሉት የአረብ ነገስታቶች የሙስሊሙ አለም ጠላቶች? የተወሰኑ ማሳያዎችን እዘረዝራለሁ በጨዋ መልኩ ሀሳብ መስጠት ይቻላል ነገር ግን አንተ ሺአ ነህ ሙናፊቅ ነህ ቅብጥርስየ ስድብ ብትሳደቡ እኔ ወንጀሌ የበዛ ሰው ነኝና ወንጀሌን እንደምታጥቡልኝ ከወዲሁ እወቁት 1 ኢራን የሙስሊሙ አለም ቀንደኛ ጠላት አይደለችም። ኢስላማዊቷ ሪፐብሊክ በተለይም በሼሪአ መተዳደር ከጀመረችበት ከኢራኑ ኢስላማዊ አብዮት ጀምሮ ስለ ሙስሊሙ አንድነት እንደወተወተች እስካሁን አለች። ኢራን የሙስሊሞች ጠላት የሆኑ አሜሪካን ጨምሮ የምዕራባውያን ጦርን በሀገሯ ያላሰፈረች ብቸኛዋ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገር ናት ። ከዚያ ይባስ ብሎ ከአካባቢው ማንኛውም የሙስሊም ጠላት የምዕራባውያን ጦር አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ እስካሁንም በብቸኝነት እየታገለች ያለች ሀገር ናት።በሙስሊም ሀገራት ላይ ኢኮኖሚያቸውንም ሆነ ወታደራዊ ሀይላቸውን ለማሽመድመድ ከምዕራባውያን ጋር የማታሴር ሀገር ናት ። 2 ኢራን አጋር ለሌላቸው እና በአረብ ሀገራት ጭምር ለምዕራባውያን እና እስራኤል ለተሸጡት ሙስሊሞች ዋና ጠበቃ ናት። የፍልስጤማውያን የቁርጥ ቀን ወዳጅ ኢራን ናት። ኢራን ባትኖር ሀማስ በዚህ ደረጃ እስራኤልን መቋቋም ይችላል ተብሎ አይታሰብም ። ሀማስን እና ኢስላሚክ ጂሀድን በአጠቃላይ ፍልስጤማዊያንን በጦር መሳሪያ እና ወታደራዊ ድጋፍ የምትረዳው ብቸኛ ሀገር ኢራን ናት ይህን እየመረራችሁም ቢሆን ዋጡት!!! ለሮሒንጊያ ሙስሊሞች ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ በማድረግ ኢራን ከቀዳሚዎቹ ናት። የጭቁን ሙስሊሞች ድምፅ እነ በመሆን እንደ ቱርክና ኳታር ሚዲያዎች ሁሉ እነደ press tv አይነቶቹ የኢራን ሚዲያወችም ተጠቃሺ ናቸው ። 3 የሙስሊም ጠላቶች ዋነኛ ጠላታቸው ኢራን ናት የኢራንም ዋነኛ ጠላቶች የሙስሊሙ ጠላቶች ናቸው። ይሆኮ ነጭ ሀቅ ነው!!! የአሜሪካ ዋና ጠላት ማን ናት ? ኢራን ናት! የእስራኤል አስፈሪዋ ጠላት ማንናት? ኢራን ናት! የአውሮፖች ቀንደኛ ጠላት ማናት ?ኢራን ናት!! ኢራንን ፈርታ እንጅ እስራኤል ጋዛንና ሊባኖስን አንድ ቀን አታሳድራቸውም። ለምዕራባውያን ባለመንበርከክ ለሙስሊሞች ምሳሌ የምትሆን ብቸኛ ሀገር ኢራን ናት 4 ኢራን የአረብ መንግስታት ጠላት ሳትሆን የአረብ መንግስታት ናቸው የኢራን ጠላቶች!! የአረብ ነገስታት በኢራን ላይ ከፈፀሙት ተቆጥሮ የማልቅ በደሎች ውስጥ -የአሜራካን ጦር በግዛታቸው በማስፈር አሜሪካ ኢራንን ለማጥቃት ያመቻት ዘንድ በኢራን ጠላትነታቸውን አሳይተዋል -ከእስራኤል ጋር በማበር ኢራንን በጋራ ለማጥቃት ሲያሴሩ ኖረዋል - ወንድማቸው ኢራን ላይ ማዕቀብ በማስጣል የነዳጅ ገበያዋን በማንኮታኮት ሀገሪቱን ለማፈራረስ ያልፈፀሙት ደባ የለም - ሳዑዲ እና አጋሮቿ አሜሪካ በኢራን ላይ ጦርነት የምትከፍት ከሆነ የአሜሪካን የጦር ወጭ ሙሉለሙሉ ለመሸፈን ቃል በመግባት አሜሪካን ሲማፀኑ ኖረዋል። ከዚህ አልፎም ከእስራኤል ጋር ጥምረት በመፍጠር ኢራንን በጋራ የሚያጠቁበትን ሁኔታ በድብቅ ሲመክሩ ኖረዋል። -ሳዳም ሁሴንን ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት ኢራንን በማስወረር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናዊያን በሰቅጣጭ ሀኔታ በመርዝ ጋዝ ጭምር በሳዳም ጦር እንዳረግፉ አድርገዋል !!ሳዳም ሁሴን ኢራንን በወረረበት ጊዜ አሜሪካ በስለላ መስሪያቤቷ በኩል ለሳዳም የኢራንን ምስጢር እየዘከዘከች ስታቀርብ የአረብ ነገስታቱ ደግሞ ዶላር ያርከፈክፉለት ነበር!! -ኢራን በሙስሊሙ አለም ውስጥ ባልሰራችው እንድትጠላ ባልፈፀመችው እንድትወቀስ በማድረግ ስሟን ጥላሸት በመቀባት ራሳቸው የሙስሊሙ አለም ቀንደኛ ጠላት ኢራንን በጠላትነት እንድትፈረጅ ከንጉሳውያን ኡለማዎቻቸው እስከ መገናኛ በዙሀናቸው ያልሰሩት የውሸት ፕሮፓጋንዳ የለም!! 5 የአረብ ነገስታት ጠላትነታቸው ለኢራን ብቻ ሳይሆን ለመላው ሙስሊም አለም ነው። -ሃፊዘልቁርአን ዶክተር ሙሀመድ ሙርሲን ከ 50 ቢሊዮን ዶላር በላይ መድበው መፈንቀለ መንግስት ከማድረግ ጀምሮ እስርቤት ውስጥ እንዲገደል ያደረጉት ኢስላምን ግብፅ ውስጥ ያቀጨጩት የአረብ ነገስታት ናቸው ። -ሊቢያን ካፈራረሷት ውስጥ የአረብ ነገስታት ከቀዳሚዎቹ ናቸው።አሁንም በቤንጋዚ መሽጎ ያለውን የሊቢያውያንን እና የሙስሊሞችን ጠላት የሆነውን ጀኔራል ኸሊፋ ሀፍታርን በሁሉም መስክ እየረዱ ያሉት እነዚሁ ነገስታት ናቸው -አሜሪካ ኢራንን እንድትወር ከመማፀን ጀምሮ ሁሉንም ድጋፍ በማድረግ ኢራቅ እንድትፈራርስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል። -ፍልስጤምን "የክፍለዘመኑ ስምምነት" (Deal of century ) በተሰኘ ስምምነት ከአሜሪካ ጋር በመስማማት ለእስራኤል የሸጡ እርኩሶች ናቸው -በሳዑዲ መሪነት የየመንን ህዝብ ጨፍጭፈዋል። ከመቶ ሺህ (100,000) በላይ የመናዊያንን ሲገድሉ ከ 27 ሚሊዮን በላይ የመናዊያን በረሀብ አለንጋ እንድገረፉ አድርገዋል ። የበርካታ ሚሊዮኖች ቤትን በጦር ጀት በማፈራረስ ቤት አልባ አድርገዋቸዋል በአጠቃላይ የመንን አፍርሰዋታል!! - በግዛታቸው የአሜሪካን ጦር በማስፈር በአፍጋኒስታን በኢራቅ በሶሪያ በፓኪስታን በየመን በአሜሪካ ጦር ለተገደሉ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ንፁሀን ሙስሊሞች ግድያ ዋና ተጠያቂ ናቸው። አሜሪካ ከምትሰራው አረመኔያዊ ድርጊት ጀር ሁሉ እነኝህ እርኩሳን የአረብ ነገስታት አሉበት !!! - በመላው አለም ሙስሊሞ በእጅጉ የሚወደደውን እና እንደ ብቸኛ የሙስሊሞች ጠበቃ የሚታየውን ረጀብ ጦይብ ኤርዶጋን ላይ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር መድበው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገዋል።አሜሪካ በቱርክ ላይ ከባድ ማዕቀብ እንድትጥል ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም። ልክ እንደ ኢራን ሁሉ ቱርክንም ሙስሊሙ አለም በጠማማነትና በጠላት እንድፈርጃት ያልሰሩት ፕሮፓጋንዳ የለም አልተሳካላቸውም እንጅ!!! - የሙስሊሞችን ኺላፋ ከማፈራረስ ጀምሮ የሙስሊሙን አለም አንድነት በመበጣጠስ የእነዚህ እርጉም ንጉሳዊያንን ያክል በሙስሊሞች ላይ በደል የፈፀመ የለም!! - በቅርቡ እንኳ ቻይና በኡይጉር ሙስሊሞች የምታደርሰውን ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ግፍና በደል እንደግፋለን እያደረገች ያለችውም ሺብርን መከላከል ነው በማለት የድጋፍ ደብዳቤ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስገብተዋል!!!ለመሆኑ ከዚህ በላይ ንፍቅና ከዚህ በላይ የሙስሊም ጠላትነት አለን???? ኢራን የሙስሊሞች ሀገር ናት ያውም 100% !! ሙስሊሟን ሀገር ኢራንን ከሙስሊሞች ብቻ አይደለም ከሰው ልጆች በሙሉ ጠላት ከሆችው አሜሪካ ጋር ከማነፃፀር በአሏህ እጠበቃለሁ! በላኢላሀኢለሏህ እና በሙሀመድ ረሱልነት የሚያምንን ፤ ለነብያቸው በፍቅር የሚያብዱን እና አህለል ቂብላ የሆኑን በአምስቱም የእስልምና መሰረቶች በስድስቱም የኢማን መሰረቶች የሚያምኑን ምንም እንኳን ታላላቅ ስህተቶች ቢኖሩባቸውም አከፍራቸዋለሁ የሚል ተክፊሪይ የማክፈር አደጋውን ለመሸከም የወደደ ነውና የስራውን ያገኘዋል !!