♥{ውድ ሥጦታ ለሚሥቶች}♥ ☞ ሚሥት ለባሏ ያላትን ፍቅር=>የምትገልፅባቸው (45) መንገዶች አዘጋጅ ሙሃመድ ዋበላǁፀሀፊ ኸድጃ ቢንት አህመድ ☞ ክፍል ① (1) ለባለቤቴ ከውጭ ወደ ቤት ሲገባ በፈገግታና በጥሩ ቃላቶች እቀበለዋለሁ..ፈገግታና ……ጥሩ_ንግግር ሰደቃ ነው ከነብዪ ሰ,ዓ,ወ) ንግግሮች "ፈገግታ የደስታ ነፀብራቅ ነው (2) ባሌ ከኔ ጋር መውጣትና መግባት በሚፈልግበት ጊዜ የቀጠሮ ሰዓቱን እጠብቅለታለሁ በማይረባነገር ጊዜውን አላጠፍበትም.. ትዳር ሰጥቶ መቀበልን ይፈልጋልና ።አንቺ እራስሽን ስጭ እርሱም እሱነቱን ይሰጥሻልና ሚስት ለባሉዋየተሰጠች ባልም ለሚስቱ የተሰጠ መለኮታዊ ጸጋዎች ናቸው (3) በተለያዪ ጊዜያት የቤት ጌጦችን በመቀያየር ላስደስተው እሞክራለሁ ።* » ሴት የባሏን ቤት ጠባቂ (ሀላፊ) ነች በጠበቀችው ነገርም ተጠየቂ ነች ።" ከነብዩሙሃመድ ;ንግግሮች። የባልሽን ስሜት አዳምጠሽና ተረድተሽ እርሱን ለማስደሰት በምታደርጊው ጥረትቅድሚያ ተጠየቂይዋ አንች ነሽ።" "① ,በአዱኒያ ያማረ ህይወት ይገጥምሻል ።② , ላደረግሽው መልካም ነገር ሁሉ በጀነት ትካሸለሽ። (4) ባሌ ከኔ ጋር በሚያወራበት ጊዜ ከፍተኛ ትኩረት እሠጠዋለሁ ከኔ ጋር በሀሳብ ሲቃረንአስተያየቱንም አከብርለታለሁ" አንድ ግለሰብ ወንድሙን በዝቅተኛ አይን ማየቱ ከወንጀል በኩል በቂ ነው ። ከነብዩ ሙሃመድ ,ሠ,ዓ,ወ )ንግግሮች ። E" ሰውን ስታከብረው የሚለውን ለመስማት ጆሮ መስጠት ትጀምራለህ።" (5) ሁሌም ከኔ እዳይሸሽ የእዝነት መንፈሴን እለግሰዋለሁ ።ምክንያቱም እሱ ልክ እንደ ህፃን ልጂጥበቃን (እንክብካቤን )ሁሌም ይፈልጋል..» በባልና በሚስት መካከል መዋደድና ፍቅር እንድኖር ከተፈለገ ርህራሄን ማሳየት ወሳኝ ነው ።» (6) "ለባለቤቴ ያለኝን ፍቅር ለመግለፅ ድገት አነስተኛ ግብዣ አድርጌ እጠብቀዋለሁ።ይህ ደግሞበመሃከላችን ያለውን ፍቅር የበለጠ ያጠናክረዋል ። »የሥጦታዎቹ ዋጋ የሚተመነው በፍቅር መገለጫነታቸው እንጅ በማነስና መብዛቱ ላይ አይደለም።« የበግ ሽኮና እንኩዋን ቢሆን መልካም ነገርን አታሳንሥ ።" ከነብዪ ሙሃመድ ንግግሮች (7) ለልጆቻችን ከፍተኛ ትኩረት መስጠቴ ለባለቤቴ ያለኝን የፍቅር ስሜት ከምገልፅባቸው መንገዶችዋነኛው ነው E ልጆችን በጥሩ ስነ ምግባር የመቅረፅና ተከባክቦ የማሳደግ ከፍተኛውን ሚና የምትጫወተው እናት ናት ።"እናት የመጀመሪያ ት/ቤት ናት ይባል የለ !! (8) " እሱን ብቻ በሚመለከቱ ነገሮች ላይ ከመግባት መቆጠቤ ለሱ ያለኝነወ ከበሬታ ከምገልፅበትመንገድ አንዱና ዋነኛው ነው*። E "ወንዶች በተፈጥሮአቸው በሴት ልጅ የመሸነፍ ባህሪ አላቸው ። ስለዚህ ሚስቶች በፀባይና በፍቅርቢይዟችው በቁጥጥር ስር የሚውሉ የዋህ ፍጡሮች ናችው።" (9) በሱ ላይ ያለኝን እምነት (መተማመን )በጥሩ ቃላቶች ደጋግሜ እነግረዋለሁ ።በተለይ ደግሞበችግርና በመከራ ሰአት ምን ያህል ታጋሸና ነገሮችን የማከናወን ብቃት እዳለው እገልፅለታለሁ።_ « የሙገሳ ቃላት የትዳርና የፍቅር ግንኙነት ዋልታና ማገሩ ናቸው ☞ ክፍል ② •° (10 ) ቅር የሚያሰኘውንና ንፁህ ህይወቱን የሚያደፈርስበትን ነገር በፉፁም አላሰማውም ።ይህንነገር ድገት ብፈፅም እንኳ እንምወደው በመግለፅ ይቅርታን እጠይቀዋለሁ። « ዓጥፍቶ ይቅርታን መጠየቅ የብልሆችና የትክክለኛ ሰዎች መስመር ነው ። … (11) ባለቤቴ ደስ እንድለው ቆንጆ ቆንጆ ልብሶችን እለብሳለሁ።እሱ የሚወዳችውን የከለር አይነቶችንእመርጣለሁ ።እሱን የሚያስደስተው ከሆነ ሜካፕም እጠቀማለሁ።» E ,አንቺ ስሜቱን ጠብቂለት እርሱ ፍላጎትሽን ሁሉ ያሟላል ይሄኔ ትዳር ያማረ ይሆናል ።" (12 ) በምግብ ሰአት ምግብ አዘጋጅቼ እርሱ በሚወደውና ደስ በሚለው መልኩ መመግቢያ ላይበማስቀመጥ አቀርባለሁ። E ድርጊት ከምናስበው እና ከምንናገረው የበለጠ የሰውን ልብ ለመማረክ ከፍተኛ ጉልበት ያለውበመሆኑ ተግባርሽ የሚበረታታነው ። (13 ) ሀሳብና ጭቀቱን እጋራዋለሁ.የገጠሙትን ችግሮች ለመፍታት ያቅሜን ያህልእምክራለሁ።ከገጠመው ችግር ለማለፍ በሚያደርገው ትግል ከጎኑ በመሆን እረዳዋለሁ ። E " ከሥጦታዎቹ የላቀው ስጦታ በችግር ሰአት የሚሰጥ ,ተሰጣጡ ትዋደዳላችሁ.. (14) በጋብቻ ቀናችን ላይ ልዪ ላዪ ስጦታ እገዛለታለሁ ።ከዚያም በኃላ በዚያ ቀን የገጠመንን የደስታናየሳቅ አጋጣሚዎች አስታውሰዋለሁ..E ስጦታ የሰውን ቀልብ የመቆጣጠር አቅሙ ከፍተኛ ነው..በስጦታ የሰውን ቀልብ መግዛት ትችላለህና ሰጭ ሁን) ከነብዪ ሙሃመድ ሰ,ዓ,ወ) ንግግሮች (15 ) ባሌ የሚወደውን ነገር አሳየዋለሁ ቅብጥብጥ እንድል አደርገዋለሁ ።ባሌ ይህን ሳደርግ ደስይለዋል ሳሻሸው ደስ እንደሚለው ሁሉ.E መልካም ሚስት ማለት የባሏ ስሜት ገብቷት ስሜቱን ለመጠበቅ የምትጥር ሴት ናት " የትዳር ህይወት ታላቅ የመተሳሰቢያ መድረክ ነው ። (16 ) መስራት ማድረግ የማልፈልገውን ነገር ባሌን ለማስደሰት ስል ብቻ አደርገዋለሁ ። ነፍሴንምከሁኔታው ጋር ለማስማማት ጥረት አደርጋለሁ..E የፍቅር አላማ የሚፈልጉትን ነገር ማግኘት ሳይሆን ለሚወዱት ሰው ደህንነት ሲሉ አንድ ቁም ነገርማድረግ ማለት ነው ።" (17)̌ " ባሌ ለኛ ሲል የሚያደርገውን ልፍትና ድካም ግምት እንምንሰጠው ስሜቴን ልገልፅለትእምክራለሁ E ሚስት ባሏን ስታሞግስና ስታመሰግነው የባሏ ልብ በሌላ መልካም ምላሽ መሰናዳቱ የማይካድ ሐቅነው መልካም ለዋለላችሁ ሰው ወረታን መልሱ ከነብዪ ሙሃመድ ሠ,ዓ፣ወ) ጣፍጭ ማህደር (18) ̌ ለባሌ የሰራሁትን ያህል ጥሩ ነገር ብሰራና ባይወድልኝ )ባይደሰትብኝ) አልበሳጭም ይህ ችግርየባሌ ብቻ ይሁን ወይስ የሁሉም ወንዶች አላውቅምE ለዚህም ስል የራሴን ስራዎች ለማሻሻል እሞክራለሁ ለማለት የፈለገች ይመስላል ☞ ክፍል ③ (19) ̌ ባለቤቴን ቤተሰቦቹ ፊት አከብረዋለሁ ሚስጥሩንም እጠብቅለታለሁ። « ባልን መታዘዝና ማክበር የአላህንና የረሱልን ሰ,ዓ,ወ, ትዕዛዝ ከመጠበቅ ይቆጠራል ።«ሚስት ባልዋን ባል ሚስቱን ማክበርና መንከባከብ ይጠበቅባቸዋል። (20) ባሌ ለኔ ምን ያክል አስፈላጊ እንደሆነ እገልፅለታለሁ።እንድሁም በስራ ቦታና በህብረተሰቡውስጥ የሱ ስራዎች ያለቸውን በጎ አስተዋጽኦ እገልፅለታለሁ።« #ሴቶች የተፈጠሩት ለወንዶች ነው ። ወንዶች የተፈጠሩት ለሴቶች ነው ። ስለዚህ አንዱ ለአንዱአስፈላጊ መሆኑን ልንቀበል የግድ ነው ። የአንድ ዛፍ ሁለት ፍሬዎች ናቸው ። (21) ባሌን እንደምወደው ደጋግሜ ያ"""",,,,,,,,, ሐቢቢ የኔ ወዳጂ በማለት እጠራዋለሁ ።ብዙ ገንዘብእንድሰጠኝ አልወተውተውም (አላስቸግረውም )። ˝ #ነብዪ ሙሃመድ ሰ,ዓ,ወ , ለአዒሻ ያላቸውን ፍቅር ለመግለፅ ሲያቆላምጧት "አዒሽ"" ብለው ይጠሯትነበር " ለባለ ትዳሮች የተሠጠ የቤት ስራ ነውና እርሶም ይሞክሩት ። (22) ከባሌ ጋር በሚኖረኝ የኑሮ ሂደት ቃል አክባሪ እሆናለሁ። አንድ አንድ ስህተቶቹን በይቅርታአልፈዋለሁ። "" በሏ እየወደዳት የሞተች ሴት እሷ የጀነት ነች "",,, ከነብዪ ሙሃመድ ሰለሏህ አለይህ ወሰለም ንግግሮች ) የባልን ደካማ ጎን ተረድታ እንደ አመጣጣቸው ለማስተናገድ የምትሞክር ሴት በእውነት ታላቅ ሴት ናት። (23) ባሌን ወዴየት እንደሚሄድ ገንዘቡን በምን መልኩ ለምን እንደሚያወጣ አልጠይቀውም ።እኔ ግንገንዘቤን ለርሱ ስል አወጣለሁ።(ገንዘቡን ሀብታችንን )ለማበራከት በሚደረገው ጥረት ተሳታፊ እሆናለሁ። በመካከላችሁ መዋደድና መተዛዘን ማድረጉ ታላቅ ታአምር ነው (24) ወደ ቤት በሚገባበት ሰአት እኳን ደህና መጣህ በማለት እቀበለዋለሁ፣እስመዋለሁ ሲናገርበወሬው እካፈለዋለሁ ።በዝምታ አላሰኘውም ) " ባለቤትሽ ወደ ቤት ሲመጣ ጥሩ አቀባበል አድርጊለት ።እርሱ የአንቺን ርህራሄና ፍቅር ሲያይ ድካም ሁሉይጠፍል ።መንፈሱ ይታደሳል። (25) አላህ /ሱ,ወ, ) ብዙ ልጆች ቢሰጠንም እርሱ ለህይወቴ በጣም አስፈላጊ መሆኑን እገልፅለታለሁ።ከዚህም ባሻገር ሙሉ ጊዜየን ለርሱ አደርጋለሁ። የሚወደውን ነገር ሁሉ አደርግለታለሁ። ǁ˝ እንደዚህ አይነቷ ሚስት ባሏን የማንበርከክ አቅሟ ከፍተኛ ነው ። (26) በውሥጤ ያለና የሚያስጨንቀኝን ነገር ሁሉ ሳልደብቅ እነግረዋለሁ ።ለርሱም ስል መስዋትነትእከፍላለሁ የተወሰኑ አቋሞቼን ለርሱ ስል እተዋቸዋለሁ ። « ግልፅ ውይይት የትዳር ማሳመሪያ መሰረታዊ መርሆ ነው " (27) የውስጥ ስሜቱ መገላበጡን (መረበሹን) ግምት አሰጣለሁ ። የሚያልፍባቸውን(የሚያጋጥሙት )አስቸጋሪ ሁኔታዎች በመረዳት እንከባከባዋለሁ በችግርም ጊዜ ከጎኑ በመቆም ድጋፌንእሰጠዋለሁ።.˝" የባሏን ሀሳብና ጭንቀት ገብቷት ከጎኑ የምትሆንን ሴት ባሎች ያከብራሉ ☞ ክፍል ④ (28) ዓላህ ሱባሀነሁ ወታአላህ እሱን እንሰሠጠኝና እሱም ህይወቴን በደስታና በመላካም ነገርእንደሞላት እገልፅለታለሁ ። እነርሱ ለናተ ልብሶች ናቸው ።እናተም ለነርሱ ልብሶች ናችሁ ቁርአን)ህይወቴን በደስታ ከሚሞሏት በርካታ ነገሮች መልካም ተስማሚ የትዳር አጋርን ማግኘት ነው። (29) የሚወደውን ነገር ሁሉ አቀርብለታለሁ እረፍት እዳገኝ እጥራለሁ ።በተለያዪ ፆታዊ ነገሮች ላይ ከኔእንድሸሽ አላደርገውመ ። ስሜቱን እጠብቅለታለሁ። (ሰዎች ለአንተ እንዳደርጉልህ የምትፈልገውም ነገርአንተም ለሰው ማድረግ ይኖርብሃል.. (30) ቤተሰባዊ ጫናዎችና ሀላፊነቶችን እንዳይከብዱት በሁሉም መልኩ እጋራለሁ። ከአቅም በላይ የሆኑ ነገሮችን በመጠየቅ አልጫነውም ። " ዓላሕ ሱባሀነሁ ወታአላ ) ባሪያውን በመርዳት ላይ ነውባሪያው ወንድሙን በመርዳት ለይ እስከሆነ ድረስ (ከነብዪ ሙሃመድ ,ሠ,ዓ,ወ) ንግግሮች (31) ቤተሰቦቹንና ጓደኞቹን አከብርለታለሁ ።በነሱም ፊት አሞግሰዋለሁ። ባልን መውደድና ማፍቀርቤተሰቦቹን ከማክበር ና ከመውደድ ጋር ይያያዛል። አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ እንዳይሆን ነገሩንበጥሞና ማየቱ ይበጃል" ዝምድና ቆራጭ የሆነ ሰው ጀነት አይገባም። ከነብዪ ሙሃመድ ,ሰ,ዓ,ወንግግሮች (32) ብቻችንን በምንቆምበት ጊዜ እጄን እጁ ላይ በማድረግ አንዳንድ ቀልዶችና ጨዋታዎችንአሰማዋለሁ ከባለቤቴ ጋር ጣፍጭ ጊዜያትን ማሳለፍ በቀላሉ ከአእምሮ የማይጠፍ ህያው ትዝታንመፍጠር መቻል ስለሆነ በትዳር ህይወት ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት ይሻል.(33) በህመሙ ጊዜ እራስጌው እቆማለሁ እሱ እዳርፍ እኔ እቅልፍ አልተኛም ።ዱአም አደርግለታለሁ ።የልብ ጓደኛ ወይም ትክክለኛ ጓደኛ የሚገለፀው በችግርና በመከራ ሰአት ከጎኑ የሚቆም ሲሆን ብቻ ነው። (34) ባሌ እኔን በሚፈልገኝ ሰአት ቀረብ ብየ በፍቅር አቅፈዋለሁ ።በተለይ አንዳንድ ነገርሲያስጨንቀውና ሲበሳጭ በማቀፍ በርሱ ያለኝን ጥሩ ስሜት እገልፅለታለሁ። ባል ሚስቱን ከጠራትለግብረ ስጋ ግንኙነት ከፈለጋት እሽ ብላ (ትምጣ) ፈቀዱን ትሙላ)። ከነብዩ ሙሃመድ ሰለሏህ አለይሂወሰለም ንግግሮች (35) ባለቤቴ የሚወዳቸውን የምግብ አይነቶች አበስልለታለሁ ።በአይነት አይነት አቀርብለታለሁ።በተለይ ጣፍጭ ነገሮችን አሳምሬ ስሰራለት በጣም ይወደኛል ። ባለቤቴን ለማስደሰት መሞከር ትዳርንከመጠበቅ ከሚደረጉ ጥረቶች ዋናው ነው ። (36) ቤተሰቦቹን በተለይ እናትና አባቱን ከማክበሬ ከማላቄ የተነሳ በመልካም ሁኔታ እኗኗራችዋለሁ።መልካም ማህበራዊ ህይወትን ለመኖር አለመታደል ሁሌም በህይወት ላይ ክፍተትን ይፈጥራል ☞ ክፍል~5 (37) ለረጅም ሰአት ከቤት ወጥቸ አልቆይም ።ከቤት በምወጣበት ጊዜ የሱን ፈቃድ እጠይቃለሁ"" ለትዳር ህይወት ደህንነት ሲባል ሚስት ያለ ባል ፈቃ ድ ከቤት መውጣት አይኖርባትም ።ስትወጣታስፈቅደው ።በአንድ ቤት ውስጥ አንድ አስተዳዳሪ መኖሩ የግድ ነው ። (38) የባሌን ሚስጥር እጠብቃለሁ። ለማንም አልናገር ።ይህንን የማደርገው ለርሱ ስል መሆኑንእገልፅለታለሁ"" የቂይያማ ቀን ከሰው ሁሉ ሸረኛና መጥፎ ማለት ከትዳር ጓደኛው ጋር የፈፀሙትን ሚስጥራዊ ነገርየሚያባክን የሚያሰራጭ ነው ።) ከነብዪ ሙሃመድ ሰ,ዓ,ወ ንግግሮች የትዳር ጓደኛን ሚስጥር ማባከን እራስንም ለውርደት የሚዳርግ ክፍ በሽታ ነው (39) ባለቤቴ ማታ ቢያመሽም እንኳ ሳልተኛ እጠብቀዋለሁ ። ሲገባም በሰላም በመምጣቱ ደስታየንእገልፅለታለሁ..."" መጥፎን ነገር በመልካም ሁኔታ መልሰው ይሄኔበአንተና በርሱ መካከል ጠላትነት ያለ ሰው እንኳ ቢሆንየቅርብ ዘመድ ወዳጅ ይሆናል (ቁርአን) (40) ባሌን በሚወደውና በሚጠላው ነገር ላይ አወራዋለሁ።ከዚያም የሚወደውን በመስራትየሚጠላውን እርቃለሁ ። ይህኔ የሱን ደስታ መሻቴን ሲያይ እኔ ለሱ ያለኝን ፍቅር ስሜት ይረዳል።ግንኙነታችንም ይበልጥ ይጠናከራል ።በደስታ የተሞላ ቤትም ይሆናል ። (41) ለባሌ እዋብለታለሁ።ከኔም ሽታ እንዲያገኝ ሽቶ እቀባለሁ። ባሌ በጥሩ ቅርፅ (ሁኔታ) እንዲያየኝእጥራለሁ። ባያመሰግነኝም ይህንን ደጋግሜ አደርጋለሁ። ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ወንዶች ብዙ አይናገሩምምስጋናም አያበዙም ስሜቶቻቸውን የሚገልፁበት ጊዜም አነስተኛ ነው (42) ለባለ ቤቴ ልጆችን እወልድለታለሁ ።ይህ አድራጎቴ እኔ ለባሌ ከፍተኛ የፍቅር ስሜት እንዳለኝይገልፅልኛል።‘“ ስታገቡ ባልዋን ወዳድና ተወዳጇን እንዲሁም ልጅ የምትወልደዋን አግቡ…"። ከነብዪ ሙሃመድ ሰ,ዓ,ወ ንግግሮች "" ልጆች የአይን ማረፊያ የልብ ደስታ። (43) ከባለቤቴ ጋር አብሬ ስሆንና ንግግር በምናደርግበት ጊዜ በየ አጋጣሚው ጉብዝናውንናወንድነቱን አገልፅለታለሁ። ጣዕም ያለው ውይይት ማለት እህ ብሎ ማዳመጥና ሀሳብን በአግባቡመግለፅም ጭምር ነው ። ህይወት በምክክር ላይ የምትገነባ ከሆነ ጣእሟ ይጨምራል ። (44) እግዶቹን በጥሩ ሁኔታ እቀበላቸዋለሁ። አከብራቸዋለሁ ።የሚቀመጡበትን ቦታም ጥሩ ሽታእንድኖረው በማድረግ አዘጋጅላቸዋለሁ። አላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን እግዳውን ያክብር ።በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ጎረቤቱን ያክብር ። በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካምይናገር ወይ ዝም ይበል ። (ከነብዪ ሙሃመድ ሰ,ዓ ,ወ ንግግሮች (45) እኔ በርሱ የረካሁ (የተብቃቃሁ)መሆኔንና ሌላ እንደማልፈልግ እገልፅለታለሁ ይህ ደግሞ ከኔጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ያጠናክርለታል በፍቅርና ርህራሄ የተሞላ ቃል በችግርና በመከራ የወደቀን ህይወት የመለወጥ አቅም አለውናቃላችንን ጠብቀን ና አስበን እንሰዝር ★ ውድ አንባቢያን ሚስቶች ከባሎቻቸው ያላቸውን ፍቅር የሚገልፁበት 45 መንገዶች በዚህአጠናቀናለ የአላህ መልካም ፈቃድ ከሆነ በቀጣይ ) ♥ {ውድ ስጦታ ለባሎች} ♥ ባሎች ሚስቶቻቸው ፍቅራቸውን እንዴት ቢገልፁሊወዱላቸው እንደሚችሉ በመግለፅ ✍ የፃፍትን 44 መንዶች በሚቀጥለው ርዕሳችን የምናይ ይሆናል……… "ዓሏህ የተግባር ሰዎች ያድርገን"" አሚን " ✿መልካም ንባብ✿ ☞ ክፍል ⑥ የዛሬዉ ርዕሥ (ባሎች) ሚስቶቻቸው ፍቅራቸውን እንዴት ቢገልፁ ሊወዱላቸውእንደሚችሉ በመግለፅ የፃፋትን ☞ (44) መንገዶች ይሆናል መልካም ንባብ" (1) ሚሥት ዓንድን ነገር ከአንድ ጊዜ በላይ በመደጋገም እየጠየቀች መጨቅጨቅ የለባትም "" ጨቅጫቃ ሚሥት ያለው ለቅነውሩን አይሄድም ።ቤቱ ለቅሶ አለውና" *በንግግርም ሆነ በተግባር ቁጥብ በመሆን የራስንም ክብር በመጠበቅ ዓላስፈለጊ ሰፍሳፋነትንምበመተው ለተሸለ ህይወት እራስን ማዘጋጀት መልካም ነው (2) ነውር ቢኖርበትም እንኳን ነውሩን መሸፈን እና በሰው ፊት አለማጋለጧ መልካም ሚስት ለመሆኗአብይ ምልክት ነው። የወንድሙን ነውር የሸፈነ አላህ ,ዓላህም (ሱ ,ወ ) የቂያማ ቀን የሱን ነውር ወይምስህተት ይሸፍንለታል ከነብዪ ሙሃመድ ሰ,ዓ ወ ንግግሮች ትወደውየራሱ ነውር አሳስቦት የሌላውን ነውር የረሳ (የተወ ለእርሱ ጀነት አለለት (3) ባሏን መታዘዟና ለመታዘዝ እሸታዋን ማሳየቷ እንድሁም የርሱን ፋለጎት መፈፀሟ እሱንእንዴምትወደው ትልቅ መልክት ነው ። መልካም ሚሥት ማለት ባላ ሲያያት የምታስደሥተው ሲያዛትየምትታዘዝ ከእርሷ ሲርቅ ገንዘቡንና ክብሯን የምትጠብቀዋ ናት !! ከነብዪ ሙሃመድ ንግግሪች መልካም ሚሥት ለባሏ ዘውድ ናት። (4)ባሏ በህይወቷ ውሥጥ በጣም ወሳኝ መሆኑን ታሳውቃለች ።በቤተሰቡና በጓደኞቹ ፊት ድርጊቷንታሳምራለች ። """ሌሎችን ለማስደሰት እራሱን የሚረሳ እና ለሎች ደስታ የሚጨነቅ የህይወትን ጣዕምያጣጥማል። ደስታንም ያገኛል Ȑ ሠውን መርዳት የደስታ ምንጭ ነው። (5) በሚያሳስቡትና በገጠሙት ችግሮች ላይ በሃሳብ መደገፍና አጋርነቷን መግለፅ አለባት መልካምሚሥት ባሏን በዱኒያም ሆነ በአኼራ ጉዳይ ላይ የምትረዳው ነች ከነብዪ ሙሃመድ ንግግሮች ችግርናመከራ ባይኖር ኖሮ እውነተኛ የህይወት ጓደኛ ማወቅ ይቸግር ነበር ። ትክክለኛ መለያው ፈተና ነው (6) _ሌሊቱ ከተጋመሠ በኃላም እንኳን ቢሆን ደክሞት ቢመጣና ጀርባውን እሸኝ ብሎ (ማሳጅ)ቢጠይቃት እሸ ብላ ትሸው. እንድሁም ጥሩ ጥሩ ቃላትን ታሠማውȐዕንኳን በሠላም መጣህ ። እኔ ምን ደርሶብሃል ብዪ ስጨነቅ ነበር። ለወደፊቱ ሥታመሽ እዳልጨነቅከቻልክ ደውለህ ነገረኝ ትበለው *ሴቶች ሠምታችዋል ☞ ክፍል ⑦" (7)..በባሏ በሥብዕና (ማንነት) መተማመንና ማክበር አለባት። ለርሷና ለልጆቿ ሲል የሚያደርገውንጥረት ዋጋ መሥጠትም ይኖርባታል።"" መልካም ነገር ለሰራለችሁ ሰው ወረታን መልሱ ካልቻላችሁ ዱአ አድርጉለት ። ከነብዪ ሙሃመድንግግሮች..(8) ..በሚሠራቸው ሥራዎችና በሚናገራቸው ንግግሮች ሳትጠራጠር እውነት ብላ ብትቀበለው ።ባትፈላፈለውና ባታውጣጣው ጥሩ ነው። መጥፎ ጥርጣሬና አወዳሚ የማይድን ደዌ ነው" ከጥርጣሬብዙውን ራቁ ቁርአን..(9) ..ያማሩና የተዋቡ ልብሶችን በመልበስ ውብ የሆኑ የሰውነት ክፍሎቿን በማሳየት እሷን በማየትእርካታና ደስታ እንድያታገኝ ታድርግ..»» ባለቤቴ እንድትጋጌጥልኝ እንደምፈልገው ሁሉ እኔም ለርሷ እጌጥላታለሁ..አብዱሏህ ቢን አባስ (10) ከባለ ቤቷ ልጆችን ለመውለድ ያላት ንፁህ ፍላጎት እርሱን ለመውደዷ አንዱ ምልክት ነው ።ከሚወዱት ሰው ልጆችን ማግኘት ትልቅ ነገር ነው የወደዱትን ሰው ምትክ በመሆን አይን ማረፊያነቱ የጎላነው «« መልካም አቀራረብና መስተግዶ የልባዊ ፍቅር ነፀብራቅ ።"" (11) በቅርብ ዘመዶቹና ጓደኞቹ ፊት እርሱን በአንድ ነገር ላይ ማማከሯ እሱን የመውደድ ምልክትነው ከመሆኑም ጋር የወንድን የሙገሳ ፈላጊነት ባህሪውን የሚያጠግብለትም ይሆናል። (12) በዓንድ ዓንድ የህይወት ጉዳዪች ላይ መስዋትነት መክፈሏ ወይም ደግሞ የተወሰኑመብቶቿን ለቤተሰቡ ደህንነትና መረጋጋት ስትል መተዋ ባሏን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስደስተው ይሆናል .. «« ግትርነት ነገርን ከማበላሸት የዘለለ ፍይዳ የለውምና ልብ በሉት (13) ለባሏ መኳኳሏና መጋጌጧ እንድሁም ለፊት የሚያገለግሉ መኳኳያዎችን እሱ በሚወደውመልኩ መጠቀሟ ፣በመነካካትና በጥሩ ንግግር ወደሱ መቅረቧ ውስጣዊ ስሜቱ ለመቆጣጣር ከፍተኛአስተዋጾኦ ያደርጋል። (14) ቤቱን በማስተዳደሩ ሚና ላይ የተፎካካሪነት ስሜቷን እና ሁሌም እሷ ከሱ በላይ ጠካራመሆኗን ለማረጋጋጥ የምታደርገዉን ሙከራ መተው አለባት። ይህን ማድረጓ በሏ በራሱ እንድተማመንየማደረግ አጋጣሚን ይፈጥርለታል«;ወንዶች በሴቶች ላይ የበላይ ጠባቂና አስተዳዳሪ ናቸው። ።ቁርአን!!! ☞ ክፍል ⑧ (15 ) ከሄደችበት ቦታ ባሏ ሳይገባ በጊዜ መመለሷ ለባሏ ያላትን ፍቅርና ከበሬታ በግልጽ የሚያሳይከበሬታ ነው።ቤቶቻችሁ እርጉ ልክ አላዋቂ ሴቶች እንደሚገላለጡት አትገላለጡ ።ቁርአን" የቤቷን ኃላፊነትለመወጣት የምትጥር ሴት ከማንም በፊት በስራዋ የምትደሰተው እርሷ ነች ባሏንም እንሰሚያስደስተውግልፅ ነው.ት"" (16)ቤቱን በማስተካከልና በማልዳቱ ላይ የበላይ ተቆጣጣሪ በመሆን መቆሟና ሙሉ ለሙሉለሰራተኛ አለመተዋ ሐላፊነቷን ያልዘነጋች ሴት መሆኗን ያመልካታልሚስት በበሏ ቤት ጠባቂ (በላፊ) ናት በጠበቀቸውም ነገር ተጠያቂ ናት ከነብዩ ሙሃመድ ንግግሮች (17) ባሏ እረፍት ፈልጎ በሚተኛበት ሰአት ከማስቸገር ተቆጥባ ልጆች እዳይረብሹ በማድግ ለማረጋጋትመጣሯ ለባሏ ያላትን አሳሳቢነትና ከበሬታ ገላጭ ነው። የሂወት አጋሩ እርካታና ደስታ እንደያገኝየሚጥርና የሚጨነቅ ከህይወት አጋሩ በፊት ደስታንና እርካታን የሚያገኘው እርሱ ነው... (18) ስትናገር ውብ የሆኑ ገለፃዎችንና ጥሩ ጥሩ ቃላትን በመምረጥ በእርጋታና ድምፅዋን ዝቅ አድርጋሳትጮህ በለዘብታ መናገሯ ብልህ ሚስት ለመሆኗ ምስክር ነው። ጣዕም ያለው ንግግር ንደት ያበርዳል።የግንኙነት መስመርም በማስተካከል ፈር እንድይዝ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል (19) በሏ በተረጋጋበት ብቻውን በተቀመጠበት ሰአት አንድ አንድ ስህተቶቹንና ነውሮቹ ላይ በሚማርክብልሃት በተሞላበት ሁኔታ።ማወያየቷ መልካም ሚስት ለመሆኗ አብይ ምስክር ነው። ሃሳብና ፍላጎትንበጥሩ ሁኔታ መግለፅ ብልህነት ነው ነገር (20) በተደጋጋሚ ገንዘብ አምጣ እያለች አትጨቅጭው።በማይመለከታት ነገርም ከመግባት ትቆጠብለሁሉም ህዝቦች የሚፈተኑበት ነገር አላቸው የኔ ኡመት (ህዝብ) መፈተኛ ገንዘብ ነው ።ገንዘብመውደድ የወንጀል ሁሉ እናት ነው ከነብዪ ሙሃመድ ንግግሮች አንድ ሰው እስልምናውአምሯል የሚባለውየማይመለከተውን ነገር ሲተው ነው ከነብዪ ሙሃመድ ንግግሮች ☞ ክፍል ⑨ǁ (21) ለርሷ ሲል ባለፍባቸው ነገሮች ልይ ልባዊ የምስጋና ቃላቶችን ብታሰማው በተለይ ከ40 አመቱበኀላ ደስ ይለዋል ምክንያቱም ወንድ ሙገሳ፣ ምስጋና ለሰራው ስራ ግምት እንድሰጠው ይፈልጋል.(22) በአጋጣሚው የሚሰቱ የህይወት ውጣ ውረዶች ከጎኑ በመቆም ረዳትነቷን ማሳየት ይኖተርባታል.. Eማንኛውም ግንኙት አስቸጋሪ የመካራ ወቅቶች ይኖሩታል። በነዚህ የችግር ወቅቶች አሳሳቢነት ፍቅርናወዳጅነትን በሚያፀባርቅ መልኩ መቅረብ የመልካም ተጓዳኞች መገለጫ ነው። (23) _ለውስጣዊና ለውጫዊ ስብዕናዊ እንዲሁም ለልጆቿ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቷና እነሱንበእክብካቤ ለማሳደግ ጥረት ማድረጓ ለባሏ ያላትን ከፍተኛ ፍቅርና አክብሮት ይገልፃል።_ *የትዳር ጓደኛውን ማስደሰት የሚፈልግ ሁሉ ለውጫዊ ስብዕናውም ትኩረት ይስጥ። (24) የባል ቤተሰቦችና የቅርብ ዘመዶች እንድወዷት ጥረት ማድረጓ ለባሏ ያላትን የፍቅር ስሜትናክብር ያሳያል..ወላጆችሽን እንደምታከብሪ የባለቤትሽን ወላጆች አክብሪያችው ። በችግርም ሆነ ደስታ ሰአት እነሱንአስቀድሚ። በምንም መልኩ አታስቀይሚያቸው ..(25) ባሏን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ከማታለል ተቆጥባ መልካም ሚስትነቷን በተግባር ማሳየትና ባልአጠገቧ ባለበትም ሆነ በሌለበት ጊዜ መጠበቅ ይኖርበታል ። ☞ ክፍል (10) (26) የባሏን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች በአግባቡ መረዳትና ራሷን ማጣጣም አለባት። የባለቤትሽንስራ ወይም የገንዘብ መጠን ይነስም ይብዛም ግምት ስጭው ።በስራው ላይ አበረታቸው ። በሚሰራውስራ ደስተኛ መሆንሽን ግለጭለት። ከባለ ቤትሽ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እራስሽን ለማስማማት ሞክሪ ባለፀጋ መብቃቃትና መሆን የውስጥ ሰላምን ይፈጥራል ..(27) „„_ ርህራሄንና ውስጣዊ ስሜቷን በመነካካትና በጥሩ ንግግር ለመግለፅ መጣደፏ በተለይከ30 አመቱ በኀላ መልካም ሚስት ለመሆኗ ግልፅ ምልክት ነው። የሙገሳ ቃላት ፍቅርንና የትዳርህይወትን ህያው አድርጎ ለማቆየት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።_(28) ""በአብዛሃኛው እራሷ የሰራቸውን ምግብ ማቅረቧ ጥሩ ነው ።ይህ ለባሏ ያላትን አሳሳቢነትናፍቅር ያሳያል። መልካም ሚስት ለትዳር ጓደኛዋ ፍይዳ ያለው ቁም ነገር ለመስራት የትዳረ ጓደኛዋን ፍላጎትማወቅ ይኖርበታል.. (29) .ቤት ሲገባ እኳን በሰላም መጣህልኝ ።ሁሌም ኑርልኝ ።አንተን በማግኘቴ ዕድለኛ ነኝ ።እኔ ካንተውጭ እንዴት እንደምኖር አላውቅም ።የሚሉና ሌሎችም መሰል ጣፍጭ ቃሎች ታሰማው (30) " ባሏ ድገት የገንዘብ ችግር ቢገጥመው ያሏትን ጌጦቸ በመሸጥ እንኳን ቢሆን በምትችለውመጠን ለመርዳት መሞከሯ ከባሏ ያላትን ከፍተኛ ፍቅር ይገልጻል። ባሏም ይህን ከፍተኘ መስዋትነትእድሜ ልኩን ሲያስታውስ ይኖራል። እርሷን ለማስደሰትና ላለመጉዳት የሚጥር ይሆናል።_ (31) ..ሚስት ከባሏ ቤተሰብ የሚመጡባትን አንዳንድ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ችላ ማሳለፍና በተቻለመጠን ችግሮች እዳይኖሩ ቀናነትን በማሳየት ተግባብታ ለመኖር መጣር አለባት._ (32) .በሏ አብሯት እያለም ሆነ ሮቆ ሲሄድ ጥርጣሬ እዳይገባውና ሰላማዊ ስሜት እንድሰማውጥረት ታደርጋለች ።ያሉበትን ሀላፊነቶች በመወጣት ላይም እገዘ ታደርጋለች ። በጎና መልካም ነገር ላይተረዳዱ.. (33) ..በፍራሽ ላይ የባለቤቷን ስሜት ለማርካት መሞከሯ እና ተስማሚ ባላሆነ ወቅት እየመጣእንደሚያስቸግራት ከመግለፅ መቆጠቧና ባሏ ስሜቱ እዳይጎዳ መጣሯ ለባሏ ያላትን ጥሩ የፍቅር ስሜት ያሳያል.. (34) "..ባለቤቴ የትምህርት ከፍተኛ " ፍላጎት ነበራት።ሆኖም አላህ (ሱ,ወ) ልጆችን ሲለግሰን አንድአንድ ፋለጎቶቿን በመተው የቤቱን ሀላፊነት ለመወጣትና ልጆችን ተከባክቦ ለማሳደግ መወሰኗ ለኔ ያላትንፍቅር የገለፀችበት አጋጣሚ በመሆኑ እድሜ ልክ የምረሳው አይሆንም .. (35) እርሱ በሚሰራቸው ስራዎችና በሚመሠርታቸው ግንኙነቶች ላይ ሁሉ ጥርጣሬዎችን አለማሳየትቀናተኝነቷን እሱን ሊያስቀይም በሚችል መልኩ አለማጸባረቅ። ቀናተኝነት ወሰን አለው ። ወሰኑን ሲያልፍመለኩን ይቀይራልና መጠቀቁ ይበጃል። ቅናት የለለው ሰው (ደዪስ) ጀነት አይገባም። ከሃድስ ማህደር።.(36) በተለያዪ ጊዜያት ለርሱ ያላትን ፍቅርና ውደታ ለመግለጽ የፍቅር ደብዳቤዎችን ብትፅፍለትግንኙነታቸውን ለማጠናከር ትልቅ እገዛ ያደርጋል ። የፍቅር ደብዳቤ በውስጣችን የተፀነሰው መጥፎስሜት በማስወገድ መልካም ግንኙነትን ይፈጥራል ።_" ☞ ክፍል ((11)) እና የመጨረሻ~ክፍል (37) ሚስት ከባሏ ጋር ጉዞ ስትወታ በአውሪፕላንም ይሁን በሌላ መጓጓዣ ሲጓዙ እጇን እጁላይ ማስቀመጧ ወይም ደግሞ ምግብ ቤት ከገቡና ባል ምግብ ካዘዛ እሷም ተመሳሳይ ምግብ ማዘዟህብረታቸውን በይፍ የምትገልፅበት ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል..(38) ባል ማታወደ ቤት ከመመለሱ በፊት ስልክ በመደወል ለእራት ምን አይነት ምግብብታዘጋጅለት እንዴሚወድ ብትጠይቀው ልቡን የመቆጣጠር አቅም ታገኛለች። ሚስቴ ስለ ደህንነቴስትጨነቅና እንደምትወደኝ ስትገልፅልኝ ውስጤ በደስታ ይሞላል ።ስራ ሁሉ ይቀናኛል ከባለ ትዳሮች አንዱ (39) ከባለቤቷ ጋር ተቀምጣ በምታወራበት ጊዜ ጠካራ ጎኖቹን ወዳወንድነቱን በመግለፅታሞግሰው። የትዳር ጓደኛን ለማስደሰት በሱ ላይ የሚታዩ ጥሩ ነገሮችን አድቁለት አነጋገርህ እንዴት ደስይላል ቁመትህ፣ ጸባይህ መልክህ፣ እና የመሳሰሉት (40), ሚስት የባለቤቷን የዕድሜ ደረጃ ግምት ውስጥ በማስገባት በዚሁ ሁኔታ ባለቤቷንመቅረብና ፍላጎቱን ማሟላት ይጠበቅባታል። ምክንያቱም ከ40 አመቱ ጋር ይለያያል። የ50 አመቱምእንደዚሁ።_ (41) _ባለቤቷ ጭማቂ ወይም ሌላ መጠጥ ሲጠጣ እሷም ባሏ ከጠጣበት የብርጭቆውክፍል (ጫፍ) መጠጣቷ ለባሏ ያላትን የፍቅር ስሜት ያንፀባርቃል። ነብዪ ሰ,ዓ,ወ ባለቤታቸው አይ ሻረ,ዐ , ከጠጣች በኀላ የሷ ከንፈር ያረፈበትን የመጠጫው ክፍል ይጠጡ እንደ ነበረ ተዘግቧል (42) ባሏ መልካም ሶላት እንድሰግድ ቁርአን እንድያነብ በተለይ ደግሞ ጁመአ ቀን ሡረቱልካህፍን እዳይረሳ ማሥታወሧ መልካም ሚስት መለሆኗ ታላቅ ምልክት ነው ። በመልካም ተግባር ላይያመለከተ እንደሰራው ይቆጠራል ። ከሀድሥ ማህደር ……………(43) ባለቤቷ ከቤት ከመውጣቱ በፊት የሚለብሰውን ልብስና ጥምጣም ጥሩ ሽታ ያላቸውንቡኽሮችና ሽቶዎች መቀባት። "" አይሻ ረ,ዐ ) ነብዪ ለሀጅ ኢህራም ከማድረጋቸው በፊትና ከሀጅ ለመፍታት ሲፈልጉ ሽቶ እቀባቸው ነበር በማለት ገልፃለች (44) ዓንድ ጊዜ ሚሥቴ በመኝታ ክፍላችን ውሥጥ በሚገኘው ትልቅ መስታወት ላይ እኔአወድሃለሁ , ብላ ጽፍ ነበር ይህ ድርጊቷን ሁሌም ዓሥታውሰዋለሁ። እህቴ ሆይ እስኪ ዓንቺምከባለቤትሽ ልብ የማይጠፍ አንድ ቁም ነገር ለመስራት ሞክሪˉ መደምደሚያ የመጨረሻ መልክት ˉ ሚሥቶችም ሆኑ ባሎች እንደዚሁም ወደ ገብቻ ፊታቸውን ያዞሩ ሰዎች በዚህ አነስተኛ መፅሀፍውሥጥ በተፃፍት ጥቂት መልክቶች ተጠቃሚ እንድሆን ከልብ እመኛለሁ ˉ በዚህአነስተኛ መፅሀፍ ምክንያት የትዳርና የቤተሰባዊ ህይወታቸውን አድሰውና አስተካክለው ፍቅርና ሰላምዘርግተው መቀራረብና ።መዛመድና ጨምረው በሠላምና በመተሳሰብ እንድኖሩ ሀያሉን አላህ ሡ ,ወ)እለምነዋለሁˉ ውድ አንባቢያን እነሆ የአላህ መልካም ፈቃድ ሆኖ ለመጨረስ በቅተናል አልሀምዱሊይላህ ሥፍርቁጥር የለለው ምስጋና ይገባህ አላህዪ በሰማነው ተጠቃሚ ተግባሪ አላህ ያድርገን ﻲﻓ ﻞﻳﺪﻌﺗ ﺮﺧآ ﻢﺗ٣٠ ،سرﺎﻣ ٢