# በመተት_የተሰናከለች_ነብስ_ክፍል 1 # እውነተኛና_አሳዛኝ_ታሪክ ሰላም ውድ አንባቢዎቼ በያላችሁበት ሰላም ለናንተ ብያለው! አሁንም ልክ እንደተለመደው አዲስ ልብ የሚነካና ለብዙ ሰዎች ትምህርት ይሰጣል ብዬ ያሰብኩትን ታሪክ ለናንተ እንዲመች አድርጌ አቀርብላችኋለው... በዚ አጋጣሚ ታሪክሽን ፍቃደኛ ሆነሽ ላካፈልሽኝ ባለታሪክ ባለሽበት አመሰግናለሁ!!! ህይወት ትባላለች የተወለደችው ውቧና የፍቅር ከተማ ከሆነችው አዳማ /ናዝሬት / ሲሆን ለቤተሰቦቿ 2ኛ ልጅ የሆነችው ህይወት ሁለት ወንድሞች አሏት። ታድያ ለህይወት ህይወት ፈተና የሆነችባት ገና በለጋ እድሜዋ ነበር ገና የ5አመት ህፃን ልጅ ሳለች ወላጅ አባቷን በሞት ተነጠቀች ይሄኔ ይህች ምንም የማታውቅ ህፃን የአባትና የእናት ፍቅርን ሳታጣጥም ከአያቶቿ ጋር መኖር ጀመረች። ይሁንና በአያት እጅ ማደግ ለህይወት ጥሩ ሆነላት እናም ልክ በ6 አመቷ ትምህርት ገባች ... ህይወት ቀልጣፋና በትምህርቷ እጅግ ጎበዝ ስለነበረች አያቷ ቅዳሜና እሁድን ሀይማኖታዊ ትምህርት ትማር ዘንድ በማሰብ ወደ ቤተክርስትያን ይልኳታል.... ህይወት በአለማዊም ሆነ መንፈሳዊ ትምህርቷ ከእድሜዋ በላይ ጎበዝ ነች ታድያ ይህች ብላቴና ማደግ አይቀርምና አድጋ የ12 አመት ልጅ ሆነች በትምህርቷም አንደኝነትን እንደያዘች 6ኛ ክፍል ደርሳለች። አንድ ቀን ህይወት የእድሜ ታላቋ ከሆነችው ግን ደግሞ በጣም ከምትወዳትና ከማትለያት ጓደኛዋ ረድኤት ጋር በአንድ ጉባኤ /የቤተ ክርስትያን ፕሮግራም/ላይ ህይወት ህፃናትን ረድኤት ደግሞ የሷ እድሜ እኩዮች የሆኑትን ታዳጊ ወጣቶች ወክለው መንፈሳዊ ስነፅሁፍ በማዘጋጀትና በማጥናት አንድ መድረክ ላይ ያቀርባሉ ይሄኔ ግን የሰውን ትኩረት የሳበችው ትንሿ ህይወት ነበረች .... ሰው ሁሉ ህይወትን እደጊ ብሎ መረቃት ያገኟት ሁሉ ሳሟት ሁሉም ወላጅ ለልጁ ምሳሌ አደረጋት ... ህይወት በደስታ ቦረቀች ይበልጥም መጎበዝ ቀጠለች... ያን የደስታ ቀንም ይበልጥ ውብ ለማድረግ የጓደኛዋ እናት እቤቷ ድረስ ምሳ በመጋበዝ በፍሬም ያማረ የድንግል ማርያምን ምስል ስጦታ አበረከተችላት ይሄ ቀን ለህይወት ሁለት ምእራፍ ነበር አንዱ በሰዎች ዘንድ ሙገሳና አድናቆት ሲሆን ላልኛውና ጥሩ ያልሆነው ደግሞ ቀላል የሚመስለው ግን ደግሞ እስካሁን ላለው ህይወቷ መበላሸት ምክንያት የሆነውን ያሬድን ያገኘችበት አጋጣሚ ነው!.... ያሬድ ያን ቀን ጓደኛዋ ቤት ሲያገኛት ወድያው ነበር የተመኛት ምንም እንኳ ህፃን ብትሆን ለሱ አላሳሰበውም ነበር ልክ ስትወጣ እንድታናግረውና እንደወደዳት ነገራት ህይወት ግን በምንም ተአምር አላወራህም ስትል መንገዱን ዘጋችው በርግጥም ይህን አይነት ህይወት ለሷ አዲስና ከሀሳቧ ውጪ ነበር ሆኖም ግን እሱ እንቢ ስትለው እጠልፍሻለውና የመሳሰሉትን ዛቻና ማስፈራርያዎችን ማስልላለፍ ጀመረ ይሄ ግትር አቋሙ ያስፈራት ህይወት ቤተሰብ ለሌላ አጭቶኛል ስትል አሳበበች እሱም እልህ ይሁን ፍቅር በማልለይ መልኩ እኔ ላግባሽ ከፈለግሽ እስክታድጊ ምንም አደድርግሽም አለ ይሄም ስላልተዋጠላት በእንቢታዋ ፀናች... ያሬድም ከቃላት ዛቻ እስከ አስገድዶ መድፈር ሙከራ አደረገባት... ይሄኔ ትምህርቷን መማር ስላቃታት የመጨረሻው አማራጯ የሄነው ለአያቷ ችግሯን ማስረዳት ነበር... ህይወት አያቷን በጣም ትወዳታለች ያለቻት ብቸኛ ሰውም እሷ ነች ለዛም ነበር ለእሷ ለመንገር የወሰነችው አያቷም ይህን ሲሰሙ ከሷ በላይ ተጨንቀው ያሬድን ካልከሰስኩ አሉ ህይወት ግን በስተርጅና አያቷ ፍርድ ቤት ለፍርድ ቤት ማለታቸውን ስላልወደደች ሌላ መፍትሄ በማሰብ አዳማን ለቃ መጥፋትን አሰበች ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ህይወት ትምህርቷን ስትማር ውላ ስትመለስ ያሬድ መንገድ ላይ ጠብቆ እያስፈራራ ሊደፍራት ይታገል ጀመር........ # ይቀጥላል ------------------........