Kedir/Fereja
-
የአደም ልጅ ሆይ! በእናትህ ሆድ ውስጥ አኖርኩህ፤ ከማሕፀን
እንዳትበረግግም ቅርፊቶችን ከፊትህ ጋረድኳቸው።
የምግቦች ጠረን እንዳይረብሽህም ፊትህን ከናትህ ሆድ ወደ
ጀርባዋ አዞርኩልህ። ከናትህ ሆድ ውስጥም ሁለት
መደገፍያዎችን አበጀሁልህ። ለቀኝህ መደገፍያ ጉበቷን አድርጌ
ለግራህ ጣፍያዋን አበጀሁልህ።
መቆምንም መቀመጥንም ከእናትህ ሆድ ውስጥ ሁነሁ
ገራሁህ፤ ታድያ ይሄን ከእኔ ሌላ እሚችል አለ?
የመውጫህ ግዜ ሲደርስማ!
መልዓኩን ልኬ ከክንፎቹ በአንዱ ላባ ቀስ አድርጎ
እንዲያስወጣህ አደረግኩ።
ሚያኝክ ጥርስ የለህ፣ እሚጨብጥ እጅ የለህ፣ እሚሮጥ እግር
የለህ...ከእናትህ ደረት ስር በሁለት ቱቦዎች የሚፈሱ ንፁህ
ወተቶችን በክረምት ሙቅ በበጋ ቀዝቃዛ አድርጌ
አመነጨሁልኽ።
ወላጆችህ ሳትጠግብ እንዳይጠግቡ፣ ሳትተኛ እንዳይተኙ
የሚያደርግ ፍቅርህን ዘራሁባቸው።
ጡንቻዎችህ ፈርጥመው ጉልበትህ የመጣ ግዜማ፤ በአመፅ
ዘመትክብኝ። ጭራሽ እኔን አታፍረኝምም።
ይህም ሁኖ!
ስትጠራኝ እመልስሃለሁ፣ ስትለምነኝ እሰጥሀለሁ፣ ተፀፅተህ
ወደኔ ብትመጣ እቀበልሃለሁ።
Il n’a plus de segments à afficher.
Chargement d’autres segments en cours…
© 2009-2024 WebTranslateIt Software S.L. Tous droits réservés.
Termes d’utilisation
·
Politique de confidentialité
·
Politique de sécurité